በፍቅር የቆዩ ጥንዶች የሚሰሯቸው ስህተቶች

በፍቅር ብዙ እየቆያችሁ ስትሄዱ አለ አይደል ሰልችቶኛል መሰለኝ ፍቅሩ ቀዝቅዟል ብለሽ የምታስቢበት ወቅት?🤔::


ፍቅር እንደ አበባ ነው:: ከተንከባከብነው ያብባል መንከባከብ ሲቆምም ይጠወልጋል:: እናም ፍቅር ይወለዳል ያድጋል ሊሞትም ይችላል ባይ ነኝ:: ፍቅር ተወልዶ ለመሞቱም ለማደጉም ትልቁ ሀላፊት ጥንዶቹ ላይ ይወድቃል:: ስህተትን ተረድቶ በቶሎ ያልታከመ ፍቅር አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም:: ይህ መልክት ጉዳዩን በማስረዳት መፍትሄ ይጦቅማል::


ቀጥሎ የጠቀስኳቸውን እያደረግሽ ከሆነ የፍቅር ሕይወትሽ አደጋ ላይ የመሆኑ ምልክት ነው::


 1. ስንገናኝ የነበረን የፍቅር ማጣፈጫ ተግባራት ማቆም

 2. የምታስቢውን እንዲያስብ የምትቀበይውን እንዲቀበል መጠበቅ

 3. ፍቅረኛን ማማት (ምስጢርን አሳልፎ መስጠት)

 4. ሀሳብን ሳይረዱ በግምት ድምዳሜ ላይ መድረስመፍትሄው ምንድነው ?

 1. ፍቅርን የሚያጣፍጡ ልምዶችን መፈጸም: አብሮ መዝናናት , ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ወዘተ...

 2. ግራ ከመጋባት መግባባትን መምረጥ ጠይቆ መረዳት አለመገመት (Ask, don’t assume)


ይበልጥ ቪድዮውን ይመልከቱ


በአሽሩካ

የይቅርታ ልብ ለሁላችን!

86 views0 comments

Subscribe to Our Newsletter

 • YouTube
 • Facebook Social Icon
 • Instagram
 • Telegram-512
 • Twitter Social Icon

Copyright © 2021 Ashruka, All rights reserved.