ዋትስአፕን የተፈታተነው ሲግናል (Signal ) አፕ ለምን ተመራጭ ሆነ ?

#ከሰሞኑ ከ2 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉትና ወደ 180 ሐገራት የሚገኙ ስዎች የሚጠቀሙት ዋትሳፕ (ዋሳፕ) (Whatsapp) መተግበርያ ያወጣው አዲስ ህግ ብዙ ተቃውሞ ደርሶበታል።


ሲግናል

የማርክ ዙከርበርግ ድርጅት እስከ የካቲት 1 (February 8, 2021) የወጣውን ህግ የማይቀበል አፑን መጠቀም አይችልም ብሏል። ይህም የግለሰብ ደህንነት ስጋት ይሆንብናል ብለው በርካቶች አፑን በመተው ሲግናል (Signal) የተባለውን አፕ ተመራጭ እያደረጉ ነው።


ለመሆኑ ሲግናል ለምን ተመራጭ ሆነ ?


👉🏾ሲግናል እንደ ዋትሳፕ መልክት መላላክያ መተግበርያ (Messaging app) ነው::

👉🏾አፑን ለመጠቀም እንደ ዋትሳፕ ስልክ ቁጥር ያስፈልጋል።

👉🏾ጽሑፍ ፣ ድምፅ እና ቪድዮ መላላክ ያስችላል::

👉ለአንድሮይድ አይ ኦ ኤስ ሲስተም በስልክም በኮምፒውተርም መጠቀም ይቻላል።

👉🏾የግለሰብ ምስጢር በመጠበቅ ወደር አይገኝለትም የሚባል ነው። ለዚህም ተብሎ በመንግስት መሰለል ስጋት የሆነባቸው ጋጤዘኞችና አክቲቪስቶች ከዚህ ቀደም በብዛት ይጠቀሙበት የነበረ አፕ ነው።

👉🏾የምትልኩትን መልክት (message) ድርጅቱም ሆነ ማንም በመሐል አይመለከተውም (uses End to end encryption)::

👉🏾የምትልኩት መልክት የትም ቦታ አይጠራቀምም ("no data on its users"):: ለምሳሌ: መረጃዎችን እያጠራቀሙ ለድርጅቶች የሚሸጡ አሉ:: ይህም ሰው ምን እንደሚወድ ምን እንደሚገበያይ ለነጋዴዎች መረጃ ይሆናል::

👉🏾ሲግናል አፕ ለትርፍ ያልተቋቋመ ነው:: የሚተዳደረውም በአለም ቀዳሚ ሀብታም የሆነው ኤለን ማስክ (Elon Musk) ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች በሚለግሱት ገንዘብ ነው::

👉ግሩፕ መፍጠር ትችላላችሁ። እንደ ቴሌግራም ግሩፑ ውስጥ ግን ያለፈቃዳችሁ ማንም ሊቀላቅላችሁ አይችልም።


👉አፑ ምርጫችሁ ከሆነ ከጉግል ስቶር (Google store)ወይም ከአፕ ስቶር (app store) “Signal” ብላችሁ በማውረድ መጠቀም ትችላላችሁ።

ፍጥጫ ላይ ያሉ ሶስቱ አፖች

ሲግናል አፕን መጠቀም ጉዳቱ (down side) ምንድነው ?👉እንደ ዋትሳፕ ብዙ ሰው ስለማይጠቀመው ለጊዜው የምትፈልጉት ሰው ላታገኙበት ትችላላችሁ።

👉ዋትሳፕ ላይ የተለመዱ የተለያዩ ፊቸሮች የሉትም።
ሲግናል አፕ የተለቀቀው በፈረንጆቹ 2014 ሲሆን ኤለን መስክ እና ሌሎች አፑን ተጠቀሙ ማለታቸውን ተከትሎ በርኮቶች ሲግናልን እየተቀላቀሉ ነው። በግሌ ሲግናልን መጠቀም ከጀመርኩ ቆይቻለው አፑ ይመቸኛል። ከሰሞኑ በርካቶች እየተቀላቀሉ ስለሆነ ብዙ ሰው እያገኘውበት ነው።